በኢትዮጵያ ተጨማሪ 30 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

63

 አዲስ አበባ ግንቦት 19/2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ 4352 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 30 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳሉት እስካሁን በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 73 1 ደርሷል።

ሚኒስትሯ እንደገለፁት ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተረጋገጠው እድሜያቸው ከ9 እስከ 60 ዓመት ነው፡፡

በምርመራ ከተረጋገጠው 22 ወንድና 8 ሴቶች ሲሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 15 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፣ 2 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው፣ 13ቱ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ወይም በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የላቸውም ተብሏል።

ሁለት ሰዎች ከትግራይ ክልል ሁሉም የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ፣8 ሰዎች ከአማራ ክልል ሁሉም የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸውና በለይቶ ማቆያ ያሉ፣ አንድ ሰው ከኦሮሚያ ክልል በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌለው፡፡

ከሐረሪ ክልል ሶስት ሲሆን ሁለቱ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው እና አንድ ሰው የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ መሆኑን ሚኒስትሯ ገልፀዋል።

በዛሬው እለት ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች 11 ዱ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 5 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው እንዲሁም 14 ሰዎች ደግሞ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው መሆናቸውን ዶክተር ሊያ በፌስቡክ ገጻቸው ይፋ አድርገዋል።

በአጠቃላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ ሰዎች 542 ናቸው።

ተጨማሪ 14 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ 181 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

አንድ ሰው በጽኑ ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገለት መሆኑም ታውቋል።

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ህብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር አሳስበዋል፡፡

እስካሁን በኢትዮጵያ አጠቃላይ 91,616 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

LikeComment

Share

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም