በጋምቤላ ክልል የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ላቦራቶሪ ስራ ጀመረ

47

ጋምቤላ (ኢዜአ) 19/2012በጋምቤላ ክልል የኮሮና ቫይረስ መመርመር የሚያስችል ላቦራቶሪ /ስራ መጀመሩን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ካን ጋሉዋክ እንደገለጹት ቀደም ሲል የነበረውን ላቦራቶሪ እንደገና በማደራጀት ለኮሮና ምርመራ የሚያገለግል ማሽን በማስገባት የምርመራ ስራው ተጀምሯል።

ላቦራቶሪው በቀን 180 ናሙናዎችን የመመርመር አቅም እንዳለው የተናገሩት ኃላፊው የኮሮና ቫይረስ የመከላከል ስራውን የተሻለ ውጤታማ እንደሚያደርገውም ተናግረዋል።

በክልሉ ቀደም ሲል የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ከግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች ጀምሮ በሙቀት ልየታና በለይቶ ማቆያ አገልግሎት የተቀናጀ ስራ ሲሰራ እንደቆየም አስረድተዋል።

ቫይረሱ ወደ ሃገራችን ከገባ ጀምሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚለዩ ሰዎችን ለቫይረሱ ተጋላጭነት ለመመርመር ናሙናዎችን ወደ አዲስ አበባ በመላክ ከፍተኛ የጊዜ ፣ የገንዘብና የሰው ኃይል ይጠይቅ እንደነበረ አስታውሰዋል።

የላቦራቶሪው ስራ መጀመር በተለይ በለይቶ ማቆያ ለሚገኙ ወገኖች ፈጣን የምርመራ አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ በድንበር አካባቢ የከናወነውን የመከላከል ስራ እንደሚያግዝም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም