በኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የግብርና ልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው

77

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 17/2012 ዓ.ም ( ኢዜአ) በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች በክልሉ ያለውን የግብርና ልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።

በጉብኝቱ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ ተሳትፈዋል።

የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮቹ ዛሬ ማለዳ በምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ መቂ ከተማ አቅራቢያ በ 2ሺህ ሄክታር መሬት ላይ እየለማ የሚገኝ የፓፓያ ክላስተር ጎብኝተዋል።

ከጉብኝቱ በኋላ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ሌንጮ ለታ በአካባቢው እየተካሄደ ያለው የግብርና ልማት ስራ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ የግብርና ልማት ስራ ወደ ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች መስፋፋት እንዳለበትም አመልክተዋል።

የክልሉ እርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ በበኩላቸው በፓፓያ ልማት ላይ የተሰማሩ የአካባቢው አርሶ አደሮች በማህበር ተደራጅተው በአዲስ አበባ ምርታቸውን ለመሸጥ የሚችሉበት ሁኔታ መመቻቸቱን ገልጸዋል።

የልማት ስራው ጉብኝት የሚቀጥል ሲሆን በአዳማ ወረዳ ሶደሬ አካባቢ የሚገኝ የአቦካዶ ተክል ልማት ይጎበኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም