የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ከምዕራብና ምስራቅ ጉጂ የተፈናቀሉ ዜጎችን እየገበኙ ነው

225
ሀዋሳ ሰኔ 29/2010 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ ሌሎችም የፌደራልና የክልል ስራ ከፍተኛ ኃላፊዎች  ከምዕራብና ምስራቅ ጉጂ የተፈናቀሉ ዜጎችን እየገበኙ ነው፡፡ ተፈናቃዮቹ የሚገኙት በጌዴኦ ዞን በ77 መጠለያ ጣቢያዎች ነው፡፡ ተፈናቃዮቹ ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከት  ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ  ለማ መገርሳ ፣ የደቡብ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተደደር አቶ ደሴ ዳልኬ እና የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር  አማን  ተገኝተዋል፡፡ የጌዲኦ ዞን ባህል ቱሪዝምና መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ታሪኩ በየነ እንደገለጹት ከጉብኝቱ በኋላም ተፈናቃዮች በሚገኙበት  ገደብ ወረዳ  ውይይት ይደረጋል፡፡ በውይይቱ በገደብ ወረዳ ያሉትን ጨምሮ ከሌሎች የመጠለያ ጣቢያዎች የተወከሉ ተፈናቃዮች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡ ውይይቱ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጭምር የሚሳተፉበት በመሆኑ ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም የተጀመረው ጥረት ለማጠናከር እንደሚያግዝም ተመልክቷል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም