ዶክተር ሊያ የካቲት 12 ሜዲካል ኮሌጅ ኮሮናቫይረስን ለመከላከል እያከናወነ ያለውን ሥራ ገበኙ

90

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12/2012 (ኢዜአ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚሰራውን ሥራ በተመለከተ በተቋሙ ጉበኝት አደረጉ።

የተቋሙ ኃላፊ ዶክተር አየለ ተሾመ ሜዲካል ኮሌጁ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል እንዲሁም መደበኛ የሕክምና ሥራውን በተመለከተ ለሚኒስተሯ ገለጻ አድርገዋል።

ሚኒስተሯም በተቋሙ ተዘዋውረው የተለያዩ የሕክምና ክፍሎችን የጎበኙ ሲሆን በተለይም ቫይረሱን ለመከላከል እየተሰራ ያለውን ሥራ ተመልክተዋል።

ጎን ለጎንም ተቋሙ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚያስፈልጉትን የሕክምናና ሌሎች ቁሳቁሶችን የተመለከቱ ሲሆን፤ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙም ከባለሙያዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

በሌላ በኩል ተቋሙ መደበኛ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥባቸውን ክፍሎች፣ የድንገተኛና የአጠቃላይ ሕክምና ክፍሎችን እንዲሁም የተቋሙን ፋርማሲ ተመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም