በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 92 ሺሕ በላይ ሆኗል

113

አዲስ አበባ  ግንቦት 13/2012 (ኢዜአ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ 1ሺሕ 792 አዲስ ሰዎች ላይ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው  የአፍሪካ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ተቋም (ሲዲሲ አፍሪካ) አመልክቷል።

 ተቋሙ እንዳመለከተው፤ በምሰራቅ አፍሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 420 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ 6 ሰዎች በዚሁ ቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸውን ሲያጡ 53ቱ ደግሞ አገግመዋል።

በመካከለኛው አፍሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ የተያዘ አለይም የሞተ እንዲሁም ያገገመ ሰው አለመኖሩም ተጠቁሟል ።

ይሁን እንጂ ባለፈው 24 ሰአታት በመካከለኛው አፍሪካ አዲስ የቫይረሱ ስርጭት ባይስተዋልም 9 ሺሕ 164 ሰዎች መይዛችው፤ 299 ሰዎች  መሞታቸውና  2 ሺሕ 522ቱ ማገገማቸውም ተጠቅሷል።

በቫይረሱ ክፉኛ በተጠቃው የሰሜን አፍሪካ ክፍል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 1ሺሕ 26 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ 22 ሰዎች በዚሁ ቫይረስ ሳቢያ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

የአፍሪካ የበሰሜን አፍሪካ ከሚገኙት ስድስት ሀገራት 29 ሺሕ 152 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ ከዚህ ውስጥ 1 ሺሕ 468 ሕይወታቸውን ሲያጡ ፣ 12 ሺሕ 392 ሰዎች አገግመዋል።

ሰሜን አፍሪካ በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚ ዞን ነው።

ሰሜን አፍሪካን አፍሪካን ተከትላ የምትገኘው ምዕራብ አፍሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 276 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ ሰባት ሰዎች ለሕልፈት ተዳርገዋል።

በምዕራብ አፍሪካ 25 ሺሕ 729 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ ከዚህ ውስጥ 9 ሺሕ 840 ሰዎች አገግመው፣ 540ዎቹ ሞተዋል።

በዓመቱ መጨረሻ 40 ሺሕ ዜጎቿን በቮይረሱ ምክንያት በሞት ትነጠቃለች የተባለችው ደቡብ አፍሪካ የምትገኝበት ደቡባዊው የአአፍሪካ ክፍል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 70 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ 6 ሰዎች አገግመዋል።

በዚህ የአህጉሪቱ ክፍል 18 ሺሕ 607 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ 8ሺሕ 385 አገግመው፣ 331ዱ ሞተዋል።

በዓለም ላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአምስት ሚሊዮን በላይ መድረሱን የዓለም ጤና ድርጅት ከደቂቃዎች በፊት በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም