የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ በይፋ ስራ መጀመሩን ገለጸ

124

 አዲስ አበባ  ግንቦት 13/2012 (ኢዜአ) የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ በይፋ ስራ መጀመሩን ገለጸ።

ፓርቲው በይፋ ስራ መጀመሩን በማስመልከት ፓርቲው ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ አመራሮችና አባላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

አባላቱና አመራሩ ቀድሞ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) አባል የነበሩና አሁን የብልጽግናን ፓርቲ የተቀላቀሉ ናቸው።

በውይይት መድረኩ የፓርቲው ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሁልና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም