በቦሰት ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ

61

አዳማ፤ ግንቦት 11/2012 (ኢዜአ) በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው ዓለሙ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ አደጋው የደረሰው በቦሰት ወረዳ ቦርጨታ ቀበሌ ላይ ዛሬ ንጋት 12  ሰዓት አካባቢ  ነው።

የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3- 00797 አፋር የሆነ ዶልፊን የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ  ከአዋሽ አርባ ወደ አዳማ በመጓዝ ላይ እያለ የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3-99458 ኢት ሲኖትራክ ጋር በመጋጨቱ ምክንያት አደጋው ሊደርስ እንደቻለ አስታውቀዋል።

በአደጋው ህይወታቸው ካለፉት አራት ሰዎች ሌላ  በአንድ ሰው ላይ ከባድ እንዲሁም በሶስት ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በቦሰት ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑንም ተናግረዋል።

የአደጋው መንስኤም ዶልፊን የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው በፍጥነት ደርቦ ለማለፍ ሲሞክር እንደሆኑ ያመለከተቱ ኮማንደር አስቻለው ፤ የሁለቱም ተሽከርካሪ ሾፌሮች ለጊዜው ከአካበቢው ሸሽተው ማምለጣቸውን አስረድተዋል።

ለጊዜው የተሰወሩትን አሽከርካሪዎች ለመያዝ ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም