ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ የቢሾፍቱ ችግኝ ዝግጅትን ጎበኙ

62

አዲስ አበባ ግንቦት 9/2012 (ኢኤአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ የቢሾፍቱ የችግኝ ዝግጅት ያለበትን ደረጃ ጎበኙ::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጪው ክረምት ለሚካሄደው የ5 ቢሊዮን ችግኝ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከሚደረገውን ዝግጅት የቢሾፍቱ የችግኝ ማፍያን ጎብኝተዋል።

ፕሪሲሽን ቴክኖሎጂን በመጠቀም እስካሁን የተደረሰበት የክንውን ደረጃ የሚደነቅ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሥራው ኢትዮጵያን አረንጓዴ ልምላሜ የማልበስ ግብን የሚደግፍ እንደሆነ መገለጻቸውን በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ይፋ አድርገዋል። ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም