የቃሊቲ አውቶቡስ ዴፖ ሊመረቅ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የቃሊቲ አውቶቡስ ዴፖ ሊመረቅ ነው
134
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6/2012 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከ789 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የቃሊቲ ዘመናዊ አውቶቡስ ዴፖ በመጪው ቅዳሜ ይመረቃል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ዴፖው ከአንድ ማዕከል ስምሪት የሚሰጥበትና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ነው።
ዴፖው በአንድ ጊዜ ከ250 እስከ 300 አውቶቡሶችን የሚያቆም ሲሆን፤ 89 አውቶቡሶችን ከመሬት በታች የማስተናገድ አቅም አለው።
በተጨማሪም ሁለት የአውቶቡስ ማጠቢያ መሣሪያዎችና አራት የነዳጅ መቅጃዎች ያለው ነዳጅ ማደያ አሉት።በአንድ ጊዜ ለ19 አውቶቡሶች የጥገና አገልግሎት የሚሰጥ ዘመናዊ ዴፖ ነው።
በተጨማሪም የአውቶቡሶች የውጭ አካል ቀለም የመቀባት አገልግሎት ሲሆን፤አንድ አውቶቡስ ከሁለት ደቂቃ ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አጥቦ የሚያደርቅ ቴክኖሎጂም ተገጥሞለታል።
በውስጡ ዘመናዊ ጋራዥን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ ህንጻዎች በዴፖው ተገንብተዋል።
ግንባታውን ሲ ኤስ ሲ ኢ የተሰኘ በቻይና የግንባታ ተቋራጭ መከናወኑን መግለጫው ያመለክታል።