በኢትዮጵያ ተጨማሪ 29 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

79

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2/2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 2171 የላቦራቶሪ ምርመራ 29 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም በኢትዮጵያ ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥርን 239 አድርሶታል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ወንድ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ዕድሜያቸውም ከ15 እስክ 45 ዓመት እንደሆኑ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል።

ቫይረሱ በምርምራ የተገኘባቸው 21 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፣ 7 ሰዎች ደግም በሶማሌ ክልል ለይቶ ማቆያ እና 1 ሰው በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ በቤት ለቤት አሰሳና ቅኝት የተለየ መሆኑን ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 2 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በአገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 99 መድረሱም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም