በላይ አርማጭሆ ወረዳ በተሽከርካሪ አደጋ ባልና ሚስትን ጨምሮ የአምስት ሰዎች ህይወት አለፈ

63

ጎንደር፤ ሚያዚያ 27/2012(ኢዜአ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ላይ አርማጭሆ ወረዳ የጭነት ተሽከርካሪ ተገልብጦ በደረሰ አደጋ ሾፌሩ፣ ባልና ሚስትን  ጨምሮ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በወረዳው ትራፊክ ፖሊስ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ማረጋገጫ ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መቅደስ ፈንታሁን ለኢዜአ እንደተናገሩት ትናንት 12 ሰዓት አካባቢ አደጋውን ያደረሰው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-46303 አዲስ አበባ የሆነ አይሲዙ የጭነት ተሸከርካሪ ነው፡፡

ተሸከርካሪው አደጋውን ሊያደርስ የቻለው በወረዳው ሮቢት ከተባለው አካባቢ ጌሾ ጭኖ ወደ ጎንደር ከተማ በማምራት ላይ እንዳለ  ወደ ኋላ ተንሸራቶ ገደል ውስጥ በመግባቱ ነው፡፡

በአደጋው ሾፎሩ ፣ባልና ሚስት እንዲሁም የሌሎች ሁለት ተሳፋሪዎች ህይወት ማለፉን  ዋና ኢንስክተር መቅደስ አስታውቀዋል፡፡ 

በአደጋው ተሽከርካሪውና  ጭኖት የነበረ ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ ንብረትም ጉዳት ደርሶበታል፡፡

አደጋው የደረሰበት መንገድ ትራፊክ ፖሊስ የማይቆጣጠረውና ከስምሪት ውጪ እንደሆነም  ዋና ኢንስፔክተሯ  ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም