በዱባይ የሚገኘው አል-ሐበሻ ሬስቶራንት ኮሮናን ለመከላከል የግማሽ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

66

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2012( ኢዜአ) ተቀማጭነቱን በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ዱባይ ያደረገው የአል-ሐበሻ ሬስቶራንት ለኮቪድ-19 መከላከል የድጋፍ ጥሪ የግማሽ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሰጠ።

የሬስቶራንቱ ባለቤቶች አቶ ሃብታሙ ደስታ እና ወይዘሮ ሳራ አራዲ ለኢዜአ እንደገለጹት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ ናቸው።

መንግስት ኮቪድ 19ን ለመከላከል ያደረገውን የድጋፍ ጥሪ ተከትሎ ከቀናት በፊት አዲስ አበባ በሚገኝ ተወካያቸው በኩል ለብሄራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ የግማሽ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

ሬስቶራንቱ ዱባይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያንን በተለያዩ መንገዶች እየደገፈና ቤት ለቤት የነጻ የምግብ አቅርቦት እያደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በቀጣይም ወረርሽኙን ለመከላከል በሚከናወነው ተግባር የዜግነት ሃላፊነታቸውን በመወጣት ከህዝብና ከመንግስት ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።

በወቅቱም የሃብት አሰባሳብ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር ምስጋናው አርጋ ”የተቋማት ድጋፍ በቫይረሱ የተቀዛቀዘውን ኢኮኖሚ የመታደግ አቅም አለው” ብለዋል።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት በመደገፍ የተለያዩ ድርጅቶች፣ ተቋማትና ግለሰቦች ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም