ባለፈው 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 745 ሰዎች ሶስቱ የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

65

አዲስ አበባ ሚያዝያ 13/2012 (ኢዜአ) ባለፈው 24 ሰዓት ውስጥ የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 745 ሰዎች መካከል ሶስት ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁለቱ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ አንዱ ቻይናዊ ነው።

ከኢትዮጵያውያኖቹ መካከል አንደኛው የጉዞ ታሪክ ያለውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ መሆኑን ገልጸዋል።

ሁለቱ ሰዎች የቅርብ ጊዜ የጉዞ ታሪክ እንደሌላቸው ተናግረዋል።

በአቃጠላይ በኢትዮጵያ ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 114 ደርሷል።

በጽኑ ህሙማን ውስጥ የሚገኝ ታማሚ የሌለ ሲሆን 93 የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

16 ሰዎች ደግሞ ማገገማቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም