የፈጠራ ባለሞያዎች የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ጥረታቸውን ቀጥለዋል

41

አዲስ አበባ ሚያዚያ 2/2012(ኢዜአ) የፈጠራ ችሎታቸውን ተጠቅመው ኅብረተሰቡን ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለመታደግ የተቻላቸውን ጥረት እያደረጉ መሆኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው የፈጠራ ባለሞያዎች ተናገሩ።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን  ለመከላላከል ዜጎች በፈጠራ፣ በዕውቀትና በገንዘብ   የተቻላቸውን አስተዋፆ እንዲያደርጉ መንግስት ጥሪ ማቅረቡ ይታወቃል።

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማምረት ላይ የሚገኙት የፈጠራ ባለሞያዋ ወይዘሮ  ብርሃኔ  በሽታውን ለመከላከል የራሳቸውን አስተዋፆ በማበርከት ላይ መሆናቸውን ይናገራሉ።

በፔዳል የሚሠራ የእጅ ማስታጠቢያና ሳሙና መጨመሪያ  የሰሩት አቶ ዮሐንስ አሸንፍ  በበኩላቸው በኮሮና ወረርሽኝ ለገጠመው  ችግር መፍትሄው ከፈጠራ ባለሙያዎች መምጣት እንዳለበት ይስማማሉ።

የመገናኛ ብዙኃን ሥራዎቹን ለተጠቃሚዎች  ከማስተዋወቅ በተጨማሪ የፈጠራ ባለሙያዎችን ማበረታታት አለባቸው ብለዋል።

ኅብረተሰቡም ከውጭ ይልቅ የአገሩን ምርት በመግዛት ፈጠራንና ባለሙያዎችን እንዲያበረታታ ጠይቀዋል።

በፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪ የምርትና ቴክኖሎጂ  ልማት  ዳይሬክተር  አቶ አሸብር አህመድ  የፈጠራና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፎችና  ባለሙያዎች  ኅብረተሰቡን   የሚጠቅሙ ምርቶችን ቢያመርቱ ይበረታታሉ ብለዋል።

በአጋጣሚው ኅብረተሰቡን እየታደጉ ገቢ ለመፍጠር እንዲሰሩም መክረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም