ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላትን በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ

57

አዲስ አበባ ሚያዚያ 2/2020 (ኢዜአ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ልዩ ስብሰባ ለኮቪድ -19 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላትን ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ በአብላጫ ድምፅ አጸደቀ፤ 

ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትና የጉዳትን መጠን ተከታትሎ በየጊዜው ለምክር ቤቱ ሪፖርት የሚያቀርብ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላትን የሰየመው ከምክርቤቱ አባላት መካከል ነው።

በእዚህ መሰረት ፡-

1ኛ - አቶ ጴጥሮስ ወልደሰንበት --- የቦርዱ ሰብሳቢ

2ኛ - አቶ ተስፋዬ ዳባ ------------የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ

3ኛ-  ወይዘሮ ፋንታዬ ወንድም -----የቦርድ አባል

4ኛ-  አቶ ሽኩሪ መሀዲን-----------የቦርዱ አባል

5ኛ-  ዶክተር ብሩክ ላጲሶ ----------የቦረድ አባል

6ኛ-  ወይዘሮ ሞሚና መሀመድ------ የቦርድ አባል

7ኛ -  አቶ በሻላ ገመቹ ------------- መርማሪ ቦርድ አባላት ሆነው ተሰይመዋል።

የአባላቱ ሹመትም በምክር ቤቱ በ12 ተቃውሞ በ5 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።

የመርማሪ ቦርድ አባላቱም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም