ግጭት ለመቀስቀስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ህብረተሰቡ በንቃት ሊጠብቅ ይገባል- የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

68
አዲስ አበባ ሰኔ 25/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በታዳጊ ክልሎች ግጭት ለመቀስቀስና ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ህብረተሰቡ በንቃት ሊጠብቅ ይገባል አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ በታዳጊ ክልሎች የእርስ በእርስ ግጭት ለመቀስቀስ እየተሰሩ ያሉ ሴራዎችን ህዝቡ ነቅቶ መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል። በመንግስት በኩል የተጀመሩ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ በየአካባቢው እየተደረጉ ላሉ ሰላማዊ ሰልፎችም ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይ ህብረተሰቡ ሰልፉን ገታ በማድረግ ሙሉ ኃይሉን ወደ ልማት ሥራዎች እንዲመልስ ጥሪ አቅርበዋል። ከዚህ በተጨማሪ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ሰላሙን ለመመለስ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተጨባጭ ስራ ለሰሩት ወገኖች ምስጋና አቅርበዋል። በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ወደ አመራር ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ያመጡትን ለውጥ በመደገፍ ሚሊዮኖች አደባባይ በመውጣት ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም