የትግራይ ክልል ምክር ቤት 6ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ ሊያኪሂድ ነው

320

መቀሌ መጋቢት 30/2012 (ኢዜአ) የትግራይ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ ሚያዝያ አንድ ቀን መጥራቱን የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት ህዝብ ግንኝነትና ኮንፍረንስ አገልግሎት ዋና የስራ ሂደት ባለቤት ገለጸ።

የስራ ሂደት ባለቤቱ አቶ ሙሉጌታ ታረቀ እንደገለጹት ምክር ቤቱ ስድስተኛ አስቸኳይ ጉባኤውን የሚያካሒደው በቪዲዮ ኮንፍረንስ ነው።

ለአንድ ቀን በሚቆየው አስቸኳይ ጉባኤ የምክር ቤቱ አባላት በወቅታዊው የኮሮና ቫይረስ መከላከልና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚመክሩ ሲሆን ለዚህም ስምንት የቪዲዮ ኮንፈረንስ ማካሔጃ አዳራሾች መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል።