ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ኮቪድ-19ን አስመልክቶ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር ተወያዩ

77

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 27/2012( ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ዙሪያ እየተወሰዱ ባሉ እርምጃዎች ዙሪያ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር በጽህፈት ቤታቸው ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎቹ ጋር ለሁለት ቀናት የሚያደርጉት ውይይት የመጀመሪያውን ዙር ዛሬ አካሂደዋል።

ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖና መንግሥት የሚወስዳቸውን ተጨማሪ እርምጃዎች አስመልክቶ የተደረገው ውይይትም ገንቢ እንደነበር አንስተዋል።

አካላዊ ርቀትን ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች በአንድ ላይ ለማግኘት ስለማይቻል  በአነስተኛ ቡድን ውይይቱ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

"በሁለተኛው ዙርና በቀጣይ  ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎቹ ጋር የምናካሄዳቸው ውይይቶችም ተመሳሳይ ውጤት እንደሚያስገኙ ተስፋ አደርጋለሁ" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም