ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር በቅርበት የሚሰሩ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ሊደረግላቸው ነው

77

መጋቢት 27/2012 (ኢዜአ) ዋይት ሀውስ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር በቅርበት የሚሰሩ ማናቸውንም ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እንዲያደርጉ  ወሰነች፡፡

ውሳኔው የተላለፈው ፕሬዝዳንቱ ለሁለተኛ ግዜ  የኮሮና ቨይረስ ምርመራ አድርገው ነጻ መሆናቸውን ተከትሎ ነው፡፡

የዋይት ሀውስ ቃል አቀባዩ ጁዴ ዴሬ እንዳሉት ትራምፕ በድጋሜ ባደረጉት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ነጻ ሆነዋል ፡፡

ይህን ተከትሎም የፕሬዘዳንቱ ና የምክትላቸው ማይክ ፔንስ ደህንነትን  ለማረጋገጥ   ከነሱ ጋር  በቅርበት የሚሰሩ ሰዎች  ምርመራ  ማድረግ አስገዳጅ ነው ብለዋል፡፡

በምርመራውም በ15 ደቂቃ ውስጥ ውጤታቸውን ማወቅ ይቻላል ነው የተባለው፡፡

በአለማችን የኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ደረጃ ከተሰራጨባቸው ሀገራት አሜሪካ አንዷ ስትሆን እስካሁን 261ሺ438 በበሽታው ተይዘዋል  6ሺ921 ሞተዋል የተቀሩት  9ሺ428 አገግመዋል ሲል የዘገበው አናዱሉ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም