የውኃ እጥረት በኮሮና ቫይረስ መከላከል ሒደት እንቅፋት እንዳይሆን አቅርቦቱን ለማሟላት እየተሰራ ነው

77

መቀለ መጋቢት 24/2012 (ኢዜአ) በትግራይ ክልል የሚታየውን የውሀ እጥረት የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በሚደረገው ጥረት አሉታዊ ተፅእኖ እንዳያሳድር ባለሃብቶች ችግሩን ለመቅረፍ እየተባበሩ መሆናቸውን የክልሉ ውሀ ሀብት ቢሮ ገለጸ።

የውሀ ሀብት ቢሮ ሀላፊ ኢንጂነር ቴዎድሮስ ገብረእግዝአብሄር እንደገለጹት በክልሉ በርካታ ከተሞችና የገጠር አካባቢዎች የመጠጥ ውሀ እቅርቦት እጥረት መኖሩን ገልጸዋል።

የኮሮና ቫይረስ አንዱ የመከላከያ መንገድ ደግሞ የእጅ ንጽህና መጠበቅ በመሆኑ ከውሀ አቅርቦቱ ጋር ያለው አለመጣጣም ፈተና መሆኑን አስረድተዋል።

ችግሩን በመገንዘብ ባለሀብቶች በክልሉ ያለውን  የመጠጥ ውሀ እጥረት ለመቅረፍ በጎ ተነሳሽነት ማሳየታቸውን  ገልጸዋል።

የመጠጥ ውሀ እቅርቦት በሌላቸው አካባበዎች ውሀ የሚያመላልሱ ሶስት ቦቴዎች በድጋፍ ተገኝቷል ።

ተጨማሪ የመጠጥ ውሀ ጉድጓድ መቆፈር በሚያስፈልጋቸው ስምንት የክልሉ አካባቢዎች ደግሞ ባለሀብቶቹ  የውሀ ጉድጓድ በነጻ ለመቆፈር ፈቃደኛ መሆናቸውን የቢሮ ሀላፊው ገልጸዋል።

የመጠጥ ውሀ እቅርቦቱ ፍትሃዊና ቆጣቢ በሆነ መንገድ ለህብረተሰቡ ለማከፋፈልና ሌሎች ስራዎችን የሚያከናውኑ ቡድኖችን ተቋቁመው ስራ ጀምረዋል ።

ከቢሮውና ከግል ባሀብቶች የተወጣጣ 12 የጥገና  ቡድኖችን በማደራጀት በክልሉ በሚገኙ ስድስት ዞኖች መመደባቸውን ገልጸዋል።

የጥገና ቡድኖቹ በየአከባቢው በብልሽት ምክንያት ውሀ ማምረት ያቆሙ የውሀ ጉድጓዶች ጥገና በማድረግ ለአገልግሎት ማብቃት ቀዳሚ ስራቸው ነው ተብሏል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም