በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ሚኒስትሮች ስለ ኮሮናቫይረስ የጥንቃቄ መልእክት አስተላለፉ

67

አዲስ አበባ፣መጋቢት 22/2012 (ኢዜአ) የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ፍጹም አሰፋ በአዲስ አበባ በመዘዋወር ስለ ኮሮናቫይረስ የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፈዋል።

የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ፍጹም አሰፋ በስድስት ኪሎ፣ አራት ኪሎና ፒያሳ አካባቢዎች በመዘዋወር የኮሮናቫይረስ ጥንቃቄ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመልእክታቸውም የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የመንግስትና የህክምና ባለሙያዎችን ትእዛዝ መተግበር ያስፍልጋል ብለዋል።

ይህ ካልሆነ ግን የሌሎች ሀገራት አሳዛኝ ገጠመኞች እኛ ላይ ላለመድርሳቸው መተማመኛ አይኖረንም ብለዋል።

የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋየ በአዲሱ ገበያና ሰሜን ሆቴል እስከ ጊዮርጊስ አካባቢ በመዘዋወር የጥንቃቄ መልእክታቸውን አድርሰዋል።

በመልዕክታቸውም የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሁሉም ድርሻ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት።

ቫይረሱ በጣሊያንና ሌሌሎች ዓለማት እያደረሰው ጉዳት በቀላሉ አለመሆኑን የገለፁት ሚኒስትሯ ቫይረሱን  ለመከላከል የሁሉንም ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅ ገልፀዋል፡፡

በመልእክታቸውም ቫይረሱ በተለያዩ ነገሮች ላይ ለረጅም ሰዓታት የሚቆይ በመሆኑ ከሰዎችና ሌሎች ነገሮች ንክኪ መራቅ ይገባል ብለዋል።የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ -19) በአለም ዓቀፍ ደረጃ የሰው ልጆችን እየፈተነ የሚገኝ ወረርሽኝ ከሆነ ውሎ ማደሩ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም