የአፍሪካ ልማት ባንክ ለዚምባቡዌ 8.2 ሚሊዮን ዶላር አበደረ

89

መጋቢት 21/2012 አፍሪካ ልማት ባንክ ለዚምባቡዌ ምግብ አምራቾች 8.2 ሚሊዮን ዶላር ብድር መስጠቱን አስታወቀ፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ በዚምባቡዌ ኦሊቫይን ኢንደስቱሪ ስር ለሚገኙ የምግብ አምራች ድርጅቶች 8.25 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሰጥቷል፡፡

ብድሩ በዋናነት ድርጅቶቹ በአዲስ መልክ  ለሚያቀርቡት የማርጋሪንና የቲማትም ምርት ማቀነባበሪያ መሳሪያዎች እድሳትና ግዢ እንደሚውል ተጠቁሟል፡፡

ምግብ ማቀነባበሪያ ማሽኖቹ ወደ ስራ ሲገቡም በቀጠናው ያለውን የምግብ ምርትና አቅርቦት አንደሚያሰድገው ታምኖበታል፡፡

‹‹በተጨማሪም ባንኩ  ለዚምባቡዌ በረጅም ጊዜ የሚከፈል የውጭ ምንዛሬ ድጋፍ እንደሚያደርግና  ይህም የፋይናስ ተቋሞቿን ለማሰደግ እና የአገሪቱን የግብርና ቢዝነስ ለማበልጸግ ትልቅ አቅም አለው›› ሲሉ የገለጹት የፍሪካ ልማት ባንክ የግብርና፣ ፋይናንስና የገጠር ልማት ዳይሬክተር አስቱኮ ቶዳ ናቸው፡፡

ባንኩ በዚምባቡዌ የግብርና ስራዎች ላይ ትልቅ እመርታ በማስመዝገብ የምግብ ዋስትናን ለማስጠበቅ፣ ለስራ ፈጠራ እና ከውጪ የሚገቡ የምግብ ምርቶችን ለመተካት  እንቅስቃሴዎች እያደረገ እንደሚገኝም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

በብድሩ በኦሊቫይን ኢንደስቱሪ ስር ያሉ ከ2 መቶ እስከ 3 መቶ ገበሬዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ተጠቁሟል፡፡  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም