በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 23 መድረሱ ተገለጸ

110

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 21/2012 በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 23 መድረሱን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።

እስከ ዛሬ ጠዋት ድረስ የላብራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው ከ800 የሚበልጡ ተጠርጣሪዎች መካከል 23 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ገልጸው፤ በቫይረሱ ህይወቱ ያለፈ እንደሌለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ሁለት ሰዎች ከህመሙ ማገገማቸውን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ቫይረሱን ለመከላከል እንዲቻል መላው የሀገሪቱ ህዝብ የሚተላለፉ የጥንቃቄ መመሪያዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ በሰጡት ወቅታዊ ማብራሪያ ቫይረሱን ለመከላከል ርብርብ ለሚያደርጉ የህክምና ባለሙያዎችና ለሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም