ጣሊያናዊው የ101 አመት የእድሜ ባለጸጋ ከኮሮና አገገሙ

109

መጋቢት 19/2012 (ኢዜአ) ጣሊያናዊው የ101 አመት የእድሜ ባለጸጋ ከኮሮና ሻይረስ ማገገማቸው ተገለጸ፡፡

እ.ኤ.አ በ1919 በተከሰተው   የስፓኒሽ ፍሉ ወቅት የተወለዱት 101 ዓመቱ የእድሜ ባለጸጋ ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

የአዛውንቱ ማገገም በወረርሽኙ የተጎሳቆለችውን ጣልያንን ተስፋ  እንድተሰንቅ አድርጓታል፡፡

ለጊዜው ሚስተር ፒ በሚል ስያሜ የሚጠሩት አዛውንቱ የጣልያኗ ሪሚኒ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ   ባሳለፍነው ሃሙስ ነበር በኮሮና ተጠቅተው ሆስፒታል የገቡት፡፡

የመቶ አንድ አመት አዛውንቱ ምንም እንካኳ በቫይረሱ ተጠቅተው ሆስፒታል ቢገቡም በጥቂት ቀናት ውስጥ  ከህመሙ ማገገማቸው ብዙዎችን አስገርሟል፡፡

የአዛውንቱ ከበሽታው ማገገምን ተከትሎ የከተማዋ ከንቲባ ግሎሪያ ‹‹ በእውነት ልዩ ክስተት ነው›› ማለታቸውን ማዘርሺፕ የተሰኘው ድረገጽ አስነብቧል፡፡

አዛውንቱ እ.ኤ.አ በ1919 በአስከፊ ሁኔታ ብዙዎችን በጎዳው የስፓኒሽ ፍሉ ወቅት መወለዳቸው ደግሞ ሌላው አስገራሚ ነገር ነው ሲሉም አክለዋል ከንቲባዋው፡፡

ከዚህ በፊት በቻይና የ100 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸው ይታወሳል፡፡

ስፓኒሽ ፍሉ ከተከሰተበት እ.ኤ.አ 1918 እስከ 1920 ድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ 50 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች መግደሉን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በጣሊያን በኮሮና ወረርሽኝ  እስከ አሁን ከ9 ሺ በላይ ሰዎች ሞተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም