በናይጄሪያ የቦንብ ፍንዳታ 100 ቤቶች፣የትምህርት ና የእምነት ተቋማትን አወደመ

61

መጋቢት 19/2012 (ኢዜአ) በናይጄሪያ የተቀበረ ቦንብ ፈንድቶ 100 ቤቶች፣ትምህርት ቤቶችና ቤተክርስቲያንን ማውደሙ ተገለጸ፡፡

በናይጄሪያዋ ኦንዶ ክፍለ አገር አኩሬ ከተማ ተቀብሮ በቆየ ቦንብ ፍንዳታ ከ100 የማያንሱ ቤቶች፣ትምህርት ቤቶች እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናት ወድመዋል፡፡

ዛሬ ጠዋት  የደረሰው የቦንብ ፍንዳታ በአኮሬ ከተማዋ   አየር ማረፊያ አቅራቢያ በሚገኘው ዋና መንገድ አካባቢ ነው፡፡

ፍንዳታው በተከሰተበት ቦታ የነበረሩ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ፈራርሰዋል ነው የተባለው፡፡

በተለይም በቤተክርስቲያን ውስጥ በነበሩት ሰዎች ላይ ጉዳቱ ሳይጨምር እንዳልቀረ የተነገረ ሲሆን  ህብረተሰቡ ጉዳቱ የደረሰባቸውን ሰዎች ለማዳን እየተረባረቡ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

ፍንዳታው ያስከተለው ጉዳት ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት የአካባቢው መንገድ መፈራረስ የእርዳታ ስራውን አስቸጋሪ እንዳደረገው ናይጄሪያን ትሪቢዩን አስነብቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም