በእንግሊዝ የግሪን ሀውስ ጋዝ ልቀት እየቀነሰ ነው ተባለ

132

መጋቢት 18/2012 (ኢዜአ) በእንግሊዝ የታዳሽ  ሃይል  አማራጮችን  መጠቀም  በመጀመሩ  የግሪን ሀውስ ጋዝ ልቀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን ክላይሜት አክሽን የተሰኘ ድረ ገጽ አስነብቧል።

እንደ ድረ ገጹ ዘገባ የሀገሪቱ  መንግሥት መረጃ እንደሚያሳየው እ.ኤ.አ. 2019 የግሪን ሀውስ ጋዝ ልቀት ከ በ2018 ከነበረው በ3.6 በመቶ ቀንሷል፡፡

 በቢዝነስ፣ ኢነርጂ እና በኢንዱስትሪ ስትራቴጂ ዲፓርትመንት የቀረበው ጊዜያዊ መረጃ እንደሚያሳየው የኢነርጂ ዘርፉ በ2019 ከፍተኛ የካርቦንዳይኦክሳይድ ልቀት ቅነሳ አሳይቷል፡፡

እ.ኤ.አ. በ1990 ከትራንስፖርት ዘርፍ ከሚወጣው የካርቦን ዳይ ኦክሳይድ ልቀት ከባለፈው የፈረንጆች ዓመት በ4.6 በመቶ ቀንሷል ተብሏል።

ለግሪን ሀውስ ጋዝ  ልቀቱ መቀነስ ዋነኛው ምክንያት መንግስት  ኤሌክትሪክን  ለማመንጨት ከድንጋይ ከሰል ይልቅ ወደ ነፋስ እና ሌሎች ታዳሽ ኃሎች ትኩረት በማድረጉ ነው ተብሏል፡፡

ጊዜያዊው መረጃ እንደሚያሳየው እ.ኤ.አ. በ2019 የእንግሊዝ ኤሌክትሪክ አቅርቦት 36.9 በመቶ ሪኮርድ ያስመዘገበ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ከነፋስ ሃይል ማመንጫ ብቻ የመጣ ነው፡፡

የእንግሊዝ የታዳሽ ሃይል ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሜላኒ ኦኔስ እንደገለጹት ይህ ሁኔታ የእንግሊዝ የኃይል ስርዓት እንዴት በከፍተኛ ሁኔታ እየተቀየረ እንዳለ ያሳያል  ብለዋል።

እንዲሁም ነፋስን እንደ ታዳሽ ሃይድሮጂን እና የባህር ኃይል ያሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እንጠቀማለን  የባትሪ ማከማቻን እናሰፋለን ብለዋል።

በአነስተኛ ወጪ ታዳሽዎች ለመንግስት የኃይል ስትራቴጂ ቁልፍ በመሆናቸው የሀገር ውስጥ አቅርቦታችን ሰንሰለት ማሳደግ ይገባል ሲሉ ተባግረዋል።

በዚህም ዘርፍ  በዓለም ዙሪያ  ብዙ ቢሊዮን ፓውንድ ወደ  ውጭ የመላክ ዕድሎችን  የምንጠቀመው በመሆኑ የእኛ ዘርፍ በቀጣዮቹ ዓመታት በፍጥነት ያድጋል ሲሉ ምክትል ስራ አስኪያጁ መናገራቸውን ክላይሜት አክሽን የተሰኘ ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም