በኮሮና የተነሳ 1.3 ቢሊዮን ተማሪዎችና 60 ሚሊዮን ገደማ መምህራን ከትምህርት ውጪ ናቸው

84

አዲስ አበባ መጋቢት 17/2012 (ኢዜአ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ባህልና የሳይንስ ተቋም ዩኔስኮ የኮሮና ወረርሽኝን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት 60.2 ሚሊዮን መምህራን እና 1.37 ቢሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

ይህም ትምህርት ከሚማሩ አራት ወጣቶች ወይም ህጻናት መካከል ሶስቱ ትምህርት ቤት እንደማይሄዱ የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ማደጉን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው በአለም አቀፍ ደረጃ ትምህርታቸውን በሚከታተሉ 80 በመቶ ተማሪዎች ላይ ተጽዕኖውን አርፏል ብሏል ዩኔስኮ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከናይጄሪያ፣ ኮስታሪካ፣ ክሮሽያ፣ ግብጽ፣ ፈረንሳይ፤ ኢራን፣ ጣልያን፣ ጃፓን፣ ሜክሲኮ እና ፔሩ እንዲሁም ሴኔጋል የተውጣጡ የትምህርት ሚኒስትሮች በችግሮ ዙሪያ እየተመካካሩ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል በችግሩ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የተለዩ በተለይም ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ ህጻናት ወደ ትምህርት የመመለስ እድላቸው አነስተኛ ነው ሲል መላምቱን ያስቀመጠው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻይልድ ፈንድ ነው፡፡

የዬኔስኮ ዋና ዳይሬክተር ሄነሪታ ፎሬ በዚህ ወቅት ‹‹የኮሮና ቫይረስ የህጻናቱን የእለት ተእለት ህይወት ባልተጠበቀ ሁኔታ ቀይሮታል፣በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ህጻናት ከትምህርት ክፍሎቻቸው ተለይተው ወራትንና ቀናትን እያሳለፉ ይገኛሉ›› ብለዋል፡:

ከከዚህ ቀደም ልምዳችን እንደምንረዳው ለበሽታው በጣም ተጋላጭ የሆኑ ልጆች ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ እድላቸው አነስተኛ ነው፣ምናልባትም ጠቂቶች ብቻ የመመለስ እድል አላቸው፣፣መልሶ ነገሮችን ለማስተካከል ከባድ መሆኑ በመግለጽ አክለዋል፡፡

ሆኖም ስራዎችን በጊዜ ማከናወን ከጀመርን ግን ዛሬን ይዘን የወደፊቱን መገንባት እንችላለን ሲሉ ችግሩ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚያስፈለግ አስገንዝበዋል፡፡

በኮሮና የተነሳ በ87 አገራት ትምህርታቸውን የቋረጡ ወጣቶችን ለማገዝ ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኤዱኬሽን ለዩኔስኮ 8.8 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ዩኔስኮ በበኩሉ ሌሎች 58 አገራትን ለመደገፍ 4 መሊዮን ዶላር መድቧል፡፡

ድጋፉም በጤናማ የትምህርት አሰጣት መንገዶች ላይ የሚያተኩር ሲሆን እንደ አእምሮ አጠባበቅ፣ አቅም ግንባታ፣ አድሎና ማግለልን በማስቀረት ተግባራት ላይ ይከናወናል ሲል ዘፐንች ዩኔስኮን ጠቅሶ አስነብቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም