በሐረሪ ከ45 ሺህ በላይ ወጣቶች በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ይሰማራሉ

62
ሀረር ሰኔ 23/2010 በሐረሪ ክልል በዘንድሮው ክረምት ከ45 ሺህ በላይ ወጣቶች በተለያዩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች እንደሚሰማሩ የክልሉ ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ቢሮ አስታወቀ። በቢሮው የወጣቶች ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታህ አብዱልከሪም ለኢዜአ እንደገለጹት ወጣቶቹ በሁለት ወራት ቆይታቸው የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት በኤች አይ ቪ መከላከልና ስነ ተዋልዶ ጤና ግንዛቤ በማስጨበጥ ተግባራት ይሳተፋሉ። የአካባቢ ጽዳትና ጥበቃ፣ ችግኝ ተከላ፣ ደም ልገሳ፣ የአረጋውያን ቤት እድሳት ጨምሮ ሌሎች የልማት ስራዎች እንደሚካሄዱ ተናግረዋል ። የሀረር ከተማ ነዋሪው ወጣት ነጂብ አሊ በሰጠው አስተያየት ላለፉት ሶስት ዓመታት የተሳተፈበትን የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ዘንድሮ አጠናክሮ ለመቀጠል መዘጋጀቱን ተናግሯል። " የበጎ ድቃድ አገልግሎት የመረዳዳት ባህልን ያዳብራል፤  የስራ ተነሳሽነትን ያጎለብታል" ያለችው ደግሞ ወጣት ጽዮን አለሙ ናት። በተለይም ዘንድሮ እየታየ ያለውን አንድነትና ፍቅርን በማጠናከር የበለጠ ለማገልገል ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም