የዓይደር ሆስፒታል ታካሚዎችን ለመጠየቅ የሚመጡ ቤተዘመዶች ማስተናገድ አቆመ

68

መቀሌ መጋቢት 11/2012 (ኢዜአ) የዓይደር ስፔሻላይዝድ አጠቃላይ ሆስፒታል ታካሚዎችን ለመጠየቅ የሚመጡ ቤተዘመዶች ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የማያስተናግድ መሆኑን አስታወቀ።

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ሪአ ኢሳያስ እንደገለጹት ሆስፒታሉ ታካሚዎችን ለመጠየቅ በየቀኑ  ከ2ሺህ በላይ ህዝብ ያስተናግዳል።

ይህም  የኮረና ቫይረስ ለመከላከል አደጋች ስለሚያደርገው ሆስፒታሉ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ  ጠያቂዎችን እንደማያስተናግድ አስታውቀዋል።

ታካሚውን የሚያስታምም አንድ ሰው እንደሚፈቀድ ጠቅሰው ለመቀያየር ሲፈልጉ ደግሞ ከውጭ የሚገባ ሰው በሙቀት መለያ መሳሪያ ታይቶ እንደሚሆን ገልጸዋል።

ሆስፒታሉ የኮረና ቫይረስ ለመከላከል ኮሚቴ አዋቅሮ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው "ማህበረሰቡ የቫይረሱን ስርጭት ለመለከላከል ንኪኪና ተሰብስቦ ማህበራዊ ጉዳዮች ከመፈጸም መታቀብ አለበት"ብለዋል።

የሆስፒታሉ ሐኪም  ዶክተር ክብሮም ገብረስላሴ በበኩላቸው በጥርጣሬ ምልክት ታይቶብናል የሚሉ ሰዎች ወደ ሆስፒታል መሄድ ሳይሆን ለዚህ  ወደ ተዘጋጀው መለስ አካዳሚ መቆያ ማዕከል  አልያም በ6244 ነጻ የጥሪ ማዕከል በመደወል አገልግሎት እንደሚያገኙ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም