በኢትዮጵያ ሦስት ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ

53

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 11/2012(ኢዜአ) በኢትዮጵያ ሦስት ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው አንድ የ44 ዓመት ጃፓናዊ ዜጋ፣ አንዲት የ85 ዓመት ኢትዮጵያዊት አዛውንት እና አንድ ኦስትሪያዊ ዜጋ በተደረገላቸው የሕክምና ክትትል እና የላብራቶሪ ምርመራ ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

አንደኛዋ ከዚህ በፊት በቫይረሱ መያዙ ከተረጋገጠ ግለሰብ ጋር ንክክ የነበራቸው የ44 ዓመት ጃፓናዊ ዜጋ ሲሆኑ እየተደረገላቸው በነበረ ክትትልና የላቦራቶሪ ውጤት በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡ ተጠቅሷል።

የ85 ዓመት እድሜ ያላቸው ኢትዮጵያዊት አዛውንት ከውጭ ከመጡ ከየካቲት 23/2012 ዓ.ም ጀምሮ እራሳቸውን ለይተው ከቆዩ በኋላ በደረገላቸው ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ነው የተረጋገጠው።

ሶስተኛው በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው የ39 ዓመት ኦስትሪያዊ መጋቢት 6/2012 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ የገቡሲሆን ፤ይህም በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎችን ቁጥር 9 ያደርሰዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም