በመዲናዋ የንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር እየተሰራጨ ነው

95

መጋቢት 8/2012 (ኢዜአ) በሀገር ውስጥ የተመረቱ የንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዘሮች በከተማዋ የከነማ መድሃኒት መሸጫዎች እየተሰራጨ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

በመሰራጨት ላይ የሚገኘው ሳኒታይዘር 200 ሺ ሊትር ያህል እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በከተማዋ በሚገኙ መድሃኒት መሸጫዎች እየተሰራጨ የሚገኘው የንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንደሚደርስም ተነግሯል፡፡

በመሆኑም ከነገ ጀምሮ ህብረተሰቡ ከከነማ ፋርማሲዎች የንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዘሮቹን በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት እንደሚቻል ከከንቲባ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም