ቤት ለቤት የሚደረግ ምንም አይነት የመድሀኒት ርጭት የለም---ከንቲባ ጽህፈት ቤት - ኢዜአ አማርኛ
ቤት ለቤት የሚደረግ ምንም አይነት የመድሀኒት ርጭት የለም---ከንቲባ ጽህፈት ቤት
102
መጋቢት 8/2012 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መኖሪያ ቤት ላይ በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ባለሙያዎች አማካኝነት የመድሀኒት ርጭት እየተካሄደ ያለ ቢሆንም ቤት ለቤት ግን ምንም አይነት የሚደረግ የመድሀኒት ርጭት የለም ብሏል።
ከንቲባ ጽህፈት ቤቱ ይህን ሽፋን በማድረግም መድሀኒት እንረጫለን በማለት የዘረፋ ወንጀሎች እየተፈጸሙ መሆኑን አስታውቆ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ገልጿል።
የመድሀኒት ርጭቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መኖሪያ ቤትና የተገለገሉባቸው ቁሳቁሶች ብቻ የሚደረግ መሆኑንና ከዚያ ውጪ ምንም አይነት የመድሀኒት ርጭት እየተካሄደ አለመሆኑ ታውቆ የከተማው ነዋሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ከንቲባ ጽህፈት ቤቱ አሳስቧል።