ከትናንት በስቲያ በአየር ጠባይ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የአገር ውስጥ በረራ ተጀመረ

91

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8/2012 መጋቢት 6 ቀን 2012 ዓ.ም በአየር ጠባይ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የአገር ውስጥ በረራ የአየር ጠባዩ በመስተካከሉ በረራው መጀመሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ።

አየር መንገዱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በረራው በመቋረጡ መንገደኞች መጉላላት አጋጥሟቸዋል።

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በረራውን ያስተጓጎለው የአየር ንብረት የተስተካከለ በመሆኑ ተጨማሪ አውሮፕላኖችን በመመደብ መጉላላት ያጋጠማቸውን ደንበኞቹን ለማስተናገድ እንደሚሰራ አየር መንገዱ ገልጿል።

በዚሁ መሰረት ከትናንት ጀምሮ በረራውን እንደቀጠለ አስታውቋል።

ወደ ደሴ የሚደረገው በረራ በአካባቢው በተከሰተው የአየር ጠባይ ለውጥ እንደተስካከለ የበረራውን መጀመር አየር መንገዱ በጥሪ ማዕከሉ በኩል ለደንበኞቹ የሚያሳውቅ መሆኑን አመልክቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መጋቢት 6 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ መቐለ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ሁመራ፣ አክሱም፣ ሽሬና ላልይበላ ሊያደርግ የነበረውን በረራ በአስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት መሰረዙን መግለጹ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም