በአዲስ አበባ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ተገኘ

83

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4/2012(ኢዜአ) በአዲስ አበባ አንድ ጃፓናዊ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የቫይረሱ ተጠቂ የ48 አመት ጎልማሳ ሲሆኑ የካቲት 25 ቀን 2012 ዓ.ም ነበር ከቡርኪናፋሶ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት።

ህብረተሰቡ ቫይረሱ ኢትዮጵያ ገባ ብሎ ከመደናገጥ ይልቅ በጥንቃቄ ከእጅ ንክኪዎች በመቆጠብና በመታጠብ እንዲሁም በርካታ ሰዎች በሚበዙባቸው አካባቢዎች ጥንቃቄ በማድረግ መከላከል እንደሚገባ መክረዋል።

የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተለያዩ የመከላከል ስራዎች እየሰሩ መሆኑንም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም