በቼዝ ውድድር ያሸነፉ ስፖርተኞች አቀባበል ተደረገላቸው

69

መቀሌ፣ የካቲት 01/2012(ኢዜአ) በሀገር አቀፍ የቼዝ ውደደር ተሳትፈው ሁለት ዋንጫዎችን ያገኙት ተወዳዳሪዎች አገራቸውን ወክለው የመወዳደር እድል በማግኘታቸው ትናንት መቀሌ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

የትግራይ ቼዝ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ መልአኩ ቴድሮስ እንደገለፁት ኢትዮጵያን ወክለው እንዲወዳደሩ የተመረጡ ሁለቱ ተወዳዳሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ከየካቲት 16 እስከ የካቲት 28 ቀን 2012 ዓም በተካሄደው አገር አቀፍ የቼዝ ውድድር በአሸናፊነት ያጠናቀቁ ናቸው።

በአዲስ አበባ በሁለቱም ፆታዎች ከሃያ ዓመት በታች በተካሄደው የቼዝ ውድድር ትግራይን ወክለው በግልና በቡድን የቀረቡ ተወዳዳሪዎች ሁለት ዋንጫዎችን በማምጣት በአንደኛነት አጠናቅቀዋል።

በግልና በቡዱን ክልሉን ወክለው የቀረቡ ማሾ በየነ እና ሮቤል ብርሃነ በኢትዮጵያ ብሄራዊ የቼዝ ቡድን ተካትተው በሱዳን በሚካሔደው  እንዲወዳደሩ በኢትዮጵያ ቼዝ ፌዴረሽን መመረጣቸውን ገልፀዋል።

ብስለትና ብቃትን በሚጠይቅ ውድድር ላይ አሸንፈው በመውጣት የሃገራቸውን መልካም ስም እንዲያስጠሩ ለማበረታታት ትናንት ማታ በመቀሌ ከተማ አቀባበል እንደተደረገላቸው አቶ መልአኩ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን ወክላ በሱዳን በሚካሔደው የአፍሪካ ዞናል አራት በአራት የቼዝ ወድድር እንድትካፈል በኢትዮጵያ ቼዝ ፌዴሬሽን የተመረጠችው ማሾ በየነ በሰጠቸው አስተያየት ትግስትና አስተዋይነትን በሚጠይቅ የቼዝ ውድድር በማሸነፍ አገሯን አስጠርታ ለመመለስ በቂ ዝግጅት ማድረጓን ገልጻለች።

በአዲስ አበባ በተካሄደው የቼዝ ማጣሪያ ውድድር ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ለወጡ የቼዝ ውድድር ስፖርተኞች ከትግራይ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ የ80 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በትግራይ ክልል የቼዝ ስፖርት ለማስፋፋት በ44 ወረዳዎች ውስጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ቼዝ ፌደሬሽን ጸሃፊ አቶ ካህሳይ ፍሳሃ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም