ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ በሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ የተሞከረውን ግድያ አወገዙ

63

አዲስ አበባ የካቲት 30/2012 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ በሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ላይ የተሞከረውን ግድያ አወገዙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት "በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ላይ የተቃጣውን የግድያ ሙከራ አወግዛለሁ" ብለዋል።

የሱዳን ሕዝብ ሠላሙን ለማስጠበቅ ከፍተኛ ዋጋ ከፍሎ የሚደነቅ እርምጃ መውሰዱንም ተናግረዋል።

እንዲህ ያሉ ክስተቶች የሱዳንን መረጋጋትና የለውጥ ጉዞ ሊያደናቅፉ አይገባም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒንስትር አቢይ በመልዕክታቸው።

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ዛሬ በሱዳን ካርቱም ከተሞከረባቸው የግድያ ሙከራ ተርፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም