ድሬዳዋ ከነማ ሃዋሳ ከተማን 3 ለ 1 አሸነፈ

61

የካቲት 29/2012 (ኢዜአ) ራሱን በአዳዲስ ተጨዋቾች ያዋቀረው ድሬዳዋ ከነማ በሜዳው ሃዋሣ ከተማን 3ለ1 ረቷል።

ደረጃውን ያሻሻለበትን ውጤት ያስመዘገበው ድሬዳዋ ከነማ ከሜዳው ውጪ ማሸነፉን ተናግረዋል፡፡

በ16ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ተጋጣሚውን ያሸነፈው ድሬዳዋ ከተማ ከተጋጣሚው ቡድን ተመጣጣኝ ፉክክር ያጋጠመው ቢሆንም ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎችን በማድረግ ውጤታማ መሆን ችሏል።

ይህንን ተከትሎ በ14ኛው ደቂቃ ሪቻርድ ኦዶንጎ የመጀመሪያውን ግብ በ40ኛው ደቂቃ ደግሞ ቢኒያም ጡዕመልሳን ማስቆጠር ችለዋል።

ከእረፍት መልስ ሃዋሳዎች ኳስን ተቆጣጥረው ግብ ለማስቆጠር ቢጥሩም ድሬዳዋ በ53ተኛው ደቂቃ ላይ ቢኒያም ለራሱ 2ተኛ ለቡድኑ ሶስተኛውን ጎል አስቆጥሮ ቡድኑ 3ለ0 መምራት ቢችልም ሃዋሳ ከተማን ከሽንፈት ያላደነችውና መስፍን ታፈሰ ባስቆጠራት አንድ ጎል ጨዋታው 3 ለ 1 ሊጠናቀቅ ችሏል።

ድሬዳዋ ከነማ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 20 ያደረሰው ሲሆን ከነበረበት 14ኛ ወደ 11ኛ ከፍ ማለት ችሏል፡፡

በመጪው አርብ ከፋሲል ጋር በሜዳው እንደሚጫወትም ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም