የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ የኤሌክትሮኒክስ ክፍያን ሊተገብር ነው

119

አዲስ አበባ የካቲት 25/2012 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኤሌክትሮኒክስ  ክፍያን ለመተግበር ከሳፕ የሶፍት ዌር ኮርፖሬሽን  ጋር እንደሚሰራ አስታወቀ፡፡

ሳፕ የተሰኘው አለም አቀፍ የሶፍትዌር ኮርፖሬሽን የአይቲ ሶፍትዌር አገልግሎቶችና በዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር ሊሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የጀርመኑ ኩባንያ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በሚፈጽመው ስምምነት ኩባንያው በቀላል የሃይል ቁጥጥር ስራ ፣በዘመናዊ የገቢ አሰባሰብ እና ክፍያ ስራዎች ላይ እንደሚሰማራ ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት   የጀመረው የፕራይቬታይዜሽን ፖሊሲ

ለሳፕ መልካም እድል  በመፍጠሩ  በዘርፉ ለመሳተፍ መወሰናቸውን  የአፍሪካ ክፍል ዋና ሃላፊ ካዚ ስሚዝ ገልጸዋል፡፡

 በቀጣይም ሳፕ በኡጋንዳ  ከሚገኙ አነስተኛና መካካለኛ ድርጅቶች ጋር በቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ እንደሚሰራ ሃላፊዋ አስረድተዋል፡፡

በአለም ካሉ ወጣቶች አብዛኛው ቁጥር በሚገኝባት የአፍሪካ አህጉር ሳፕ በዲጂታል አገልግሎት ላይ ትኩረቱን አድርጎ በቀጣይ እንደሚሰማራ ማስታወቁን ያስነበበው ብሉንበርግ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም