በኬንያ በየአመቱ 10ሺ ታዳጊዎች ትምህርታቸን በእርግዝ ያቋርጣሉ

121

 የካቲት 24/2012 (ኢዜአ) 10ሺ ኬንያውን ታዳጊዎች  በእርግዝና  በየአመቱ  ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ ተባለ ፡፡

በአገሪቱ የተደረገ ጥናት እንዳመለከተው  የታዳጊዎች  እርግዝናና እና እናትነት እየጨመረ መጥቷል፡፡

 በጥናቱ መሰረትም ከ15 እስከ 19 ዓመት እድሜ ክልል ከሚገኙት አምስት ታዳጊዎች አንዷ ታረግዛለች አለያም የመጀመሪያ ልጇን ወልዳለች፤ይህም ችግሩን አስከፊ አድርጎታል ነው የተባለው፡፡

 በ15 አመታቸው የሚያርግዙ ሴቶች ሶስት በመቶ ሲሆኑ የታዳጊዎቹ እድሜ ወደ 19 ዓመት ከፍ ሲልም  የእርግዝና መጠኑ  ሶስት ከመቶ  ወደ 40 በመቶ ማደጉ ተነግሯል፡፡

የችግሩ ስፋትም ከቦታ ቦታ ይለያያል ያለው ጥናቱ፣ ናሮክ የተባለው አካባቢ በ40 በመቶ፣ሆማባይ 33 በመቶ፣ ምዕራብ ፖኮት 29 በመቶና ታና ወንዝ አካባቢ እርግዝና ከሚከሰትባቸው ቦታዎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው ተብሏል፡፡

50 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ እርግዝናውን ለማስወረድ በሚያደርጉት ሙከራ ህይወታቸው እንደሚያልፍ ተገልጿል፡፡

በኬንያ የታዳጊዎች እርግዝና በአርብቶ አደር አካባቢዎች  በስፋት የሚታይ ሲሆን አላቻ ጋብቻ፣ በእውቀት ማነስ፣ እንዲሁም የወሊድ መቆጣጠሪያ መድኃኒቶች እጥረት ለችግሩ መንስኤ መሆናቸውን የኬኒያው ካፒታል ኤፍኤም አስነብቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም