በባህሬን የኢፌዲሪ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ለመክፈት ዝግጅት በመደረግ ላይ ነው

51

የካቲት 24/ 2012 (ኢዜአ)  በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ የልኡካን ቡድን ዛሬ በባህሬን የኢፌዲሪ የቆንስላ ጽህፈት ቤት መክፈት በሚቻልበት ገዳዮች ዙሪያ ለመምከር ባህሬን ከተማ ገብቷል።

የቆንስላ ጽህፈት ቤቱ የሚከፈተው የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ በመካከለኛ ምስራቅ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በቅርቡ በዱባይ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ባህሬን ላይ የተፈጠረውን ችግር አስመልክተው በሰጡት አቅጣጫ መሰረት ነው።

የልዑካን ቡድኑ አባላት በባህሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በኩዌት የኢፌዲሪ አምባሳደር አብዱልፋታህ ሃሰን እና በባህሬን የኢፌዲሪ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ተወካይ ወይዘሮ እስከዳር ግርማይ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ቡድኑ በቆይታው በባህሬን ከሚኖሩ የተለያዮ የማህበረሰቡን አባላት ጋር በጋራና በተናጠል የሚያወያይ ሲሆኑ፤

እንዲሁም  ከባህሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር በባህሬን ያሉ ዜጎቻችን መብት፤ ጥቅም እና ደህንነት በሚጠበቅበት ዙሪያ ውይይት ያደርግል።

በተጨማሪም ሁለቱን አገሮች በሚያስተሳስሩ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያገኘነው መረጅ ያሳያል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም