በደቡብ ኮሪያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ መጠን እየተስፋፋ ነው

55

የካቲት፣ 21/2012 (ኢዜአ) በደቡብ ኮሪያ የኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ መጠን እየተሰራጨ መሆኑን ቢቢሲ ዘገበ።

በዘገባው እንደተመለከተው በደቡብ ኮሪያ በአንድ ቀን ብቻ 594 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

በአገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 931 መድረሱን የኮሪያ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል ማስታወቁን ዘገባው አስታውሷል።

የ17 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ሳቢያ ማለፉም ተገልጿል።

በአለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ከተስፋፋባቸው አገራት መካከል ደቡብ ኮሪያ ከቻይና ቀጥሎ እንደምትገኝ በዘገባው ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም