ከ11 አመት በኋላ ማህጸኗ እንደሌለ ያወቀችው እንስት ጉዳይ

75

የካቲት 20/2012 ይህ የሆነው ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ነው።ወይዘሮ ሚስቢ የተባለች እንስት የመጀመሪያ ልጇን የወለደችው በ17 አመቷ ነው። በዛን ጊዜ ነበር ወደ ማደንዘዣ ክፍል ተወስዳ ሳትጠየቅና ይሁንታዋን ሳትሰጥ ለመውለድ በሄደችበት ሆስፒታል ማህጸኗ እንዲወጣ የተደረገው።

ድርጊቱ የተፈፀመው በሀገሪቱ የመንግስት ሆስፒታል ውስጥ ሲሆን ሚስቢ በደቡብ አፍሪካ ይህን መሰል ድርጊት ከተፈጸመባቸው ሴቶች መካከል 48ተኛዋ መሆኗን ቢቢሲ ገልጿል።

ይህን ያረጋገጠው ደግሞ በሀገሪቱ በጾታ እኩልነት ዙሪያ የሚሰራ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው፡፡ድርጀቱ  በ15 የመንግስት ሆስፒታሎች ላይ ባደረገው የታካሚዎች ፋይል ምርመራ በመንግስት ህክምና መስጫ ተማቋት ድርጊቱ እንደሚፈጸም አረጋግጧል ፡፡

የደቡብ አፍሪካ ጤና ሚኒስቴር እስካሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ የሰጠው ዝርዝር ማብራሪያ ባይኖርም ጉዳዩን አስመልክቶ ከኮሚሽኑ ጋር ውይይት እንደሚያደርግ ግን ገልጿል።

ወይዘሮ ሚስቢ ለቢቢሲ እንዲህ ትላለች ለወሊድ ወደ ህክምና ስገባ አስታውሳለሁ፤ እስክወልድ ድረስ ሰመመን ውስጥ ነበርኩ፣ የነቃሁት ልጄን ከተገላገልኩ በኋላ ነው።

እንደነቃሁ ወዲያውኑ ወደ ሆዴ ተመለከትኩ፤ሆዴ ላይ ትልቅ ስፌት  አየሁ ምንድን ነው ይህ ስልም ሃኪሞችን ጠየቅሁ፤ በሰዓቱ መልስ የሚሰጠኝ አላገኘሁም፡፡እኔም ብዙ ትኩረት አልሰጠሁትም ነበረ።

ልጄ ስትወለድ ትልቅ ሆና ነበር፤ ማለቴ ወፍራም፤ወልጄ አምስት ቀን እንደሞላኝም ከሴት ህጻን ልጄ ጋር ወደ ቤቴ ተመለስኩ፡፡ ማህጸኔ መውጣቱን ያወኩት ግን ከወለድኩ ከአስራ አንድ አመት በኋላ ነው፡፡

እውነት ለመናገር እስከዛ ድረስ ጠባሳው ከመኖሩ ውጭ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረኝም፡፡ነገሩን ያወኩት ሁለተኛ ልጅ ለመውለድ ወደ ሃኪም ቤት ባቀናሁበት ወቅት ነበር፡፡

የመጀመሪያ ልጄን ከወለድኩበት ጊዜ ጀምሮ የእርግዝና መቆጣጠሪ መድሃኒት እጠቀም ነበር፡፡ከእለታት በአንዱ ቀን ነበር ድጋሜ ልጅ ለመውለድ ወደ ጤና ጣቢያ ያቀናሁት፡፡ ያኔ ነበር ዶ/ሩ ማህጸን እንደሌለኝ የነገረኝ፡፡

እንዲህ ሲለኝ  ግራ ገባኝ፡፡ ውስጤንም ምን ማለቱ ነው ሲል ጠየኩት።ከዚህ በፊት ልጅ መውለዴንና እናት መሆኔን ሳስብ ደግሞ ነገሩ  እጀግ ግራ አጋባኝ፡፡ ማህፀኔ ተወግዶ ከሆነ የመወገድ አደጋው ሊከሰት የሚችለው ብቸኛው ጊዜ በወሊድ ወቅት ነው ስል አሰብኩ።ምን አይነት ጭካኔ ነው በኔ ላይ የተሰራው ስልም አሰብኩ፡፡

ጉዳዩን ይዤ ወደ ሚዲያ ወጣሁ ፡፡ከትንሽ ጊዜ ቆይታ በኋላ ማህጸኗን ያስወገደው  ያዋለዳት ዶ/ር መሆኑን ሊሆን እንደሚችል አሰበች፡፡ ወዲውኑም ሚስቢ ወደ ሆስፒታሉ በማቅናት ያዋለዳትን ደ/ር  ለምን ማህጸኔን ያለ እኔ ፈቃድ አስወገድከው? የሚል ጥያቄ አቀረበችለት፡፡

ዶክተሩም ማህጸንሽን ያስወገድኩት ህይወትሽን ለማትረፍ ነው፤ ማህጸንሽ ባይወገድ አንች አትተርፊም ነበር ሲል ምለሽ ሰጣት፡፡

ሚስቢን መልሱ አሳማኝ ካለመሆኑ በተጨማሪ ይቅርታ አለመጠየቁ እጀግ አስቆጣት፡፡

ሚስቢ ከሆስፒታሉ በሰዓቱ እኔን ለሞት ሚያበቃ የሚያሳይ ምንም አይነት ማስረጃ አልተገኘም ፤ስለዚህ የዚህ ሰውዬ እኔን ከየትኛው ሞት እንዳዳነኝ አልተገለጠልኝም ትላለች፡፡

"ይህ ማህጸን የማስወገድ  ድርጊት በኔ ብቻ የደረሰ አይደለም፡፡በተመሳሳይ በሌሎች 47 ሴቶች ላይ ተፈጽሟል፡፡ነገር ግን የኔውን ለየት የሚያደርገው ምንም አይነት ለሞት የሚያበቃም ሆነ ለሌላ ችግር የሚያጋልጥ ኬዝ አለመገኘቱ ነው፡፡የሌሎች ማህጸን የማስወገድ ድርጊት የተደረገው ኤች-አይ-ቪ ኤዲስ በደማቸው ውስጥ ስለተገኘባቸው ነው፡፡በዛ ላይ  በፈቃዳቸው ያስደረጉት ነው።የእኔ ግን የተለየ ነው ምክኒያቱም ኤች-አይ-ቪ ኤዲስም ሆነ ሌላ በህይወቴ ላይ ከባድ አደጋ የሚያደርስ በሽታ አልተገኘብኝም" ትላለች ሚስቢ በምሬት ለቢቢሲ ስትናገር፡፡

" በዚህ ምክኒያት ከባለቤቴ ጋር ተለያየን ፡፡ እሱን በእውነት መተው ነበረብኝ ምክንያቱም እሱ  ልጆችን መውለድ ይፈልጋል እኔ ደግሞ ይህን ማድረግ አልቻልኩም" ብላለች፡፡

"ይህ በእውነት ኢ-ሰባዊ ድርጊት ነው ፣ከትዳሬ አለያየኝ ፣ልጄንም ያለ እህትና ወንድም አስቀረ" ትላለች።

በመጨረሻም ይህ ያለባለቤት ፈቃድ የሚፈጸም፣ ባልን ያለሚስት፣ ሚስትን ያለባል ልጅን ያለ እህት / ወንድም የሚያስቀር ህገ ወጥ-ተግባር በሚፈጽሙ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ ተገቢው ቅጣት ሊተላለፍባቸው እንደሚገባ ገልጻለች፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም