የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን በጅቡቲ ብሔራዊ ቀን ተሳተፈ

79
አዲስ አበባ ሰኔ 21/2010 ጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን በጅቡቲ ብሔራዊ ቀን ላይ ተሳተፈ፡፡ የዲፕሎማሲ ቡድኑ የተሳተፈው ጅቡቲ ከቅኝ ግዛት የወጣችበትን 41ኛ ዓመት ሰኔ 20 ቀን 2010 ዓ.ም. በድምቀት ባከበረችበት ወቅት ነው፡፡ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድኑ በበዓሉ ላይ በመታደም ከጅቡቲ ህዝብ ጋር ያለውን አጋርነት አሳይቷል፡፡ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ በበዓሉ ማብቂያ የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ልዑካን ቡድኑን በብሔራዊ ቤተ-መንግስት መጋበዛቸውም ተጠቁሟል፡፡ በተመሳሳይ ልኡኩ ከጅቡቲው  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሀመድ አሊ ዩሱፍ ጋር  በባህል፣ በትምህርት፣ በቢዝነስ፣ በንግድና በወደብ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይቷል፡፡ በተጨማሪም ልዑካን ቡድኑ ጅቡቲ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ተገናኝቶ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክሯል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም