ሶማሊያ 330 ሚሊዮን ዶላር ዕዳ ተሰረዘላት

92

አዲስ አበባ የካቲት 19/2012 ( ኢዜአ)  ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት /አይ.ኤም.ኤፍ/ የሶማሊያን የ330 ሚሊዮን ዶላር ዕዳ እንደሰረዘላት አስታወቀ።

ለአገሪቷ ዕዳው የተሰረዘላት በድርጅቱ ድጋፍ የሚከናወነውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ ግብር ለማገዝ ነው።

ሶማሊያ የፋይናንስ ዘርፍ ማስተካከያዎችን ለማድረግ ያላትን ተነሳሽነትና የገጠሟትን ችግሮች ለመወጣት የምታደርገው ጥረት ስረዛው እንዲደረግላት ያደረጉ ምክንያቶች መሆናቸውም ተገልጿል።

በዓለም ድሃ ከሚባሉ አገራት አንዷ የሆነችው ሶማሊያ በድርጅቱ የሚደገፍ የኢኮኖሚ መርሐ ግብር በማካሄድ ላይ ትገኛለች።

ሶማሊያ 5 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ እንዳለባት የእንግሊዝ ዜና ማሰራጫ ድርጅት (ቢቢሲ) ዘገባ ያመለክታል።

አገሪቷ ባለፉት ዓመታት በዓለም ሙሰኛ ከሚባሉ አገራት ተርታ መቀመጧ ይታወሳል።