ናይጄሪያ ግዙፍ የሃይል ማመንጫ ግድብ ልትገነባ ነው

197

የካቲት 19/2012 (ኢዜአ) ናይጄሪያ ለኤሌክትሪክ ማመንጫ የሚሆናትን ግድብ ታሪባ በተባለው ግዛቷ ውስጥ ባለው  ዶንጋ ወንዝ ላይ ልትገነባ ነው

ግንባታው ሲጠናቀቅ 3 ሺህ 50 ሜጋ ዋት ያመነጫል ተብሎ የሚታሰበው ይሄ ግድብ በስፋቱም ሆነ በአቅሙ ከታላቁ የኢትዮያ ሀዳሴ ግድብ ቀጥሎ በአፍሪካ ሁለተኛው ገዙፍ ግድብ ይሆናልም ተብሏል።

ግድቡ የሚያመነጨው ሃይል የናይጄሪያን ሩብ የሃይል ፍላጎት የሚያሟላ መሆኑን ያነሳው ዘገባው፤  4.8 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ወጪ በቻይና ኩባንያዎች የሚገነባ መሆኑን ተጠቅሷል

ፕሬዝዳንት ሙሃሙዱ ቡሃሪ  የናይጄሪያን የሃይል እጥረት ለመፍታት ያስቀመጡትን አቅጣጫ መሰረት በማደረግ ቻይናውያኑ ኩባንያዎች በቅርቡ ወደ ግንባታው ይገባሉ ያለው ዘገባው እድሜ የተጫናቸው የሃይል መሰረተ ልማቶችም በአዲስ እንደሚተኩም ተጠቅሷል

ብዙዎቹ የናይጄሪያ የሃይል አቅራቢ ኩባንያዎች ደካማ የሃይል ስርጭት ያላቸው እንደሆነ የጠቀሰው ዘገባው ፤ ሀገሪቱ  ከምታገኘው   13 ሺህ ሜጋ ዋት ሃይል 80 በመቶ የሚሆነው ጋዝ በሚጠቀሙ ጄኔሬተሮች የሚመረት  መሆኑን ጠቅሶ የዘገበው ፓምፕስ አፍሪካ ድረገጽ ነው