ሳኡዲ ኮሮና መፍትሄ እስኪያገኝ ድረስ ወደ መካ መዲና የሚደረግ ጉዞን አገደች

99

የካቲት 19/2012 (ኢዜአ) የሳኡዲአረቢያ መንግስት ሃይማኖታዊ ጉዞን ጨምሮ በማንኛውም ጉዳይ  ወደ ሳውዲ  የሚደረጉ ጉዞዎችን ማገዷ ተሰማ፡፡

ኮሮና ቫይረስ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ብቻ 220 ሰዎችን ተጠቂ ማድረጉ ከተሰማ በኋላ ሳኡዲንም ስጋት ውስጥ ከቷታል፡፡

እገዳው   በየጊዜው ከተለያዩ አለም ሀገራት 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ሰዎች ወደ መካ መዲና የሚያደርጉትን ጉዞ እንደሚያጠቃልል ተነግሯል፡፡

በዚህም ምክንያት በየአመቱ  የሚካሄደው ጉዞ ሊራዘም እንደሚችል እየተነገረ  ነው ፡፡

ሆኖም ሰአውዲ አረቢያ እደስካሁን በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ሰው ያልተገኘባት ሀገር ነች፡፡

የሳውዲ መንግስት የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል በሚደረገውን ጥረት ሁሉ ለመደገፍ ዝግጁነቱ መሆኗ ተነግሯል፡፡

(አልጀዚራ)

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም