በመቀሌ ከተማ በደረሰው የትራፊክ አደጋ ሶስት ሰዎች ሞቱ

59

መቀሌ ኢዜአ የካቲት 18/2012 ዓ/ም በመቀሌ ከተማ በዓዲ-ሓ ቀበሌ ዛሬ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ትራፊክ ፖሊስ ገለፀ ።

በከተማው የሐውልት ክፍለ ከተማ ትራፊክ ፖሊስ ዋና ሳጅን ለምለም መንገሻ እንደገለፁት ዛሬ ረፋድ ላይ የትራፊክ አደጋ ያጋጠመው ሲኖ ትራክ የጭነት መኪና ከአንድ ለማጅ ባጃጅ ጋር በመጋጨቱ ነው።

በተፈጠረው የትራፊክ አደጋ ለሞት የተዳረጉ ሰዎች አስከሬን  ቤተሰቦቻቸው እንዲረከቡ እየተደረገ መሆኑን ዋና ሳጅኗ ገልፀዋል ።

ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ሰዎች ደግሞ ወደ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ተልከው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው ብለዋል ።

ባለፈው ሳምንትም በአከባቢው 52 ሰው የጫነ ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በፍጥነት እያሽከረከረ እያለ ተገልብጦ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉን ከዋና ሳጅን ለምለም መንገሻ ገለፃ ለማወቅ ተችሏል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም