በደቡብ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ስልጠና ተጀመረ

66

ሐዋሳ  የካቲት 17/2012 (ኢዜአ) በሀገሪቱ የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማጠናከር የሚያግዝ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ስልጠና በደቡብ ክልል 14 ማዕከላት ተጀመረ።

የደቡብ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ስልጠናው  ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ሲጀመር እንደገለጹት በለውጡ ዙሪያ ግልፀኝነት በመፍጠርና የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ታግሎ በማሸነፍ ሀገሪቱንና   ህዝቦቿን ወደ ብልፅግና  የሚያመጣ አመራር ለማፍራት እየተሰራ ነው።

የአመራሮቹ ስልጠና መረሀ ግብር  ለ11 ቀናት የሚቆየው ክልል አቀፍና ሀገሪቱን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር የሚደረገው እንቅስቃሴ አካል መሆኑን አመልክተዋል።

በክልሉ 14 ማዕከላት በሚሰጠው በዚሁ ሥልጠና  ከ13ሺ በላይ አመራሮች እንደሚሳተፉ ገልጸው ለስልጠናው አምስት የመወያያ ሰነዶች መዘጋጀታቸውን ጠቅሰዋል።

ሰነዶቹ በለውጡ ምንነትና የተወሰዱ እርምጃዎች ፣ በፓርቲው ርዕዮተ ዓለምና አንድምታዎች ፣ ብልጽግናን የማረጋገጥ ትልምና ፈተናዎቹ እንዲሁም በቀጣዮቹ አስር  ዓመታት የብልፅግና መሪ ዕቅድ ላይ ያተኮሩ መሆናቸው አስታውቀዋል ፡፡

ሥልጠናው በፓርቲው ውስጥ ያሉ አመራሮች በሪፎርሙ ላይ የተሟላ ግልፀኝነት ፈጥረው በለውጡ ሂደት ውስጥ በቀጣይ በሚኖሩ መሰረታዊ አቅጣጫ ላይ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ  ለመድረስ ታስቦ መዘጋጀቱን አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም