ኬንያ ከኢትዮጵያ የአትክልት ምርት መግዛት መጀመሯ ተነገረ

68

የካቲት 17/2012 (ኢዜአ) በኬንያ የሸቀጦች ዋጋ በባለፈው ወር በእጥፍ መጨመሩን ተከትሎ ኬንያውያን ነጋዴዎች ከኢትዮጵያ የቲማቲም ምርት እየገዙ እንደሚገኝ ተነገረ፡፡

በኬንያ ለተከሰተው የቲማቲም ምርት እጥረት መከሰት የአየር ንብረት ለውጥ  ዋናውን ቦታ እንደሚይዝ ተነግሯል፡፡

የቲማቲም ዋጋ በኢትዮጵያ ውድ በመሆኑ ነጋዴዎቹ ምርቱን  በመግዛት  ውድ  ሀገሪቱ ማስገባት ቢጀምሩም  አሁንም   በኬኒያ የናረውን  ዋጋ ማረጋጋት አልተቻለም ነው የተባለው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ምርቱ  በሚጓጓዝበት ወቅት ስለሚበላሽ ነጋዴዎቹን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስት ከቷቸዋል፡፡

ኬንያ በየዓመቱ ከ 4መቶ ሺህ ቶን  በላይ  የአትክልት  ምርቶችን   ታመርታለች  ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም